የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የስራ ኃላፊው በፖሊስ ተያዙ!

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዢ ቡድን መሪ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በ300 ሺህ ብር የሙስና ወንጀል የተጠረጠረን የመንግስት የስራ ኃላፊና በንግድ ስራ ላይ የተሰማራን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎች አቶ ዓለም ተ/ኃማኖት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የግዢ ቡድን መሪ እና አቶ ሳሙኤል መላኩ የተባሉ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰብ ሲሆኑ፤ አቶ ዓለም ተ/ኃይማኖት በቢሮአቸው ለሚፈፀመው የችግኝ ጣቢያ ግብዓቶች ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም በወጣ ጨረታ አቶ ሳሙኤል መላኩ ጨረታውን አሸንፈዋል፡፡

ተከሳሽ አቶ ሳሙኤል መላኩም ከአቶ ዓለም ተ/ኃይማኖት ጋር በቀጣይ በቢሮው በሚቀርቡ የግዢ ሂደቶችና ጨረታዎች ላይ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ያልተገባን ድርድር በማድረግ ለቢሮው ግዢ ቡድን መሪ የሦስት መቶ ሺህ ብር ቼክ በሚሰጡበት ወቅት አስቀድሞ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የክትትና የምርመራ ቡድን ጥናት ሲደረግባቸው በመቆየቱ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል ብሏል፡፡
*

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...