የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ግሪንላንድ ከዴንማርክ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታቋርጥ አሳሰቡ

Date:

አወዛጋቢውን የአሜሪካ ግሪንላንድን የመጠቅለል ግስጋሴ ሲቀጥል የዩናይትድ ስቴይስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ደሴቲቱ ከዴንማርክ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት እንድታቋርጥ እና በምትኩ ከዋሽንግተን ጋር አጋር እንድትሆን ጥሪ አቅርበዋል። ዴንማርክ በግሪንላንድ ኢንቨስት እያደረገች ነው ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሰሜናዊ ግሪንላንድ የሚገኘውን የርቀት የዩናይትድ ስቴትስ ፒቱፊክ የጠፈር ጣቢያን ባደረጉት አጭር ጉብኝት ቫንስ እንዳሉት “በምድር ላይ ያለች ብቸኛዋ የግሪንላንድ ሉዓላዊነት እና ደህንነታቸውን የምታከብር ሀገር አሜሪካ ነች” ብለዋል።

ዴንማርክ “በግሪንላንድ ህዝብ ላይ ኢንቨስት አድርጋችኋል እናም በዚህ አስደናቂ ውብ መሬት ደህንነት ላይ ኢንቨስት አድርጋችኋል” ሲሉም ለዴንማርክ  ተናግረዋልል። ቫንስ ተጨማሪ የህዝብ ቦታዎችን ቢጎበኝ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው ሪፖርቶች ከወጡ በኋላ የመጀመሪያውን የጉዞ እቅድ ሰርዘዋል። ቫንስ ከዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ እና የኢነርጂ ፀሀፊ ክሪስ ራይት ጋር በመሆን በደሴቲቱ ላይ ያለውን የአሜሪካ ሰራዊት ቆይታ ለመጨመር ፈጣን እቅድ ዋሽንግተን የላትም ነገር ግን የባህር ሃይል መርከቦችን እና ወታደራዊ የበረዶ መንሸራተቻዎችን ጨምሮ ተጨማሪ ሀብቶችን እንደሚመድቡ ተናግረዋል ።

19 ዲግሪ ሴልሺየስ ቅዝቃዜ ባለበት በግሪን ላንድ፣ የቫንስ ጉብኝት ለጥቂት ሰአታት ብቻ የቆየ ነበር።የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄንስ ፍሬድሪክ ኒልሰን ጉብኝቱ “ለግሪንላንድ ሕዝብ አክብሮት እንደሌለው ያሳያል” ብለዋል። የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚቲ ፍሬድሪክሰን ሀገሯ የአርክቲክ  መከላከያ ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳደገች በመግለጽ፣ አዳዲስ የስለላ ስርዓቶችን እና የረጅም ርቀት አውሮፕላኖችን እንዲሁም መርከቦችን ጨምሮ ማሰማራቷን በማንሳት የአሜሪካን አስተያየት  ውድቅ አድርገዋል።”ለበርካታ አመታት ከአሜሪካውያን ጎን ለጎን ቆመናል” ስትል ተናግራለች። “ስለዚህ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዴንማርክን የሚያመለክቱበት ትክክለኛ መንገድ አይደለም” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሯ አክለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...