የዩክሬን ከፍተኛ የመረጃ ባለስልጣን በቀን ኪዬቭ ላይ በጥይት ተደብደበው መሞታቸው ተወስቷል፡፡
የዩክሬን የአገር ውስጥ ደህንነት አገልግሎት (ኤስ ቢ ዩ ) ወኪል ማንነቱ ባልታወቀ ተጠርጣሪ በተደጋጋሚ መመታቱ የተነገረ ሲሆን ገዳዩ ከአካባቢው ለቆ ሲሄድ የሚያሳዩ መረጃዎች በመውጣት ካይ ናቸው።
ወደ ሟቹ አጥቂው ከቀረበ በኋላ ጥቃቱን እንደሰነዘርውም ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የስለላ ድርጅቱ የሟቹን ማንነት ይፋ ባያደርግም መገናኛ ብዙሃን “ኮሎኔል ኢቫን ቮሮኒይች “ናቸው በሚል እያስነበቡ ነው፡፡
ኤስ ቢ ዩ የአገር ውስጥ ደህንነት እና መረጃ ላይ የሚሰራ ቢሆንም ወደ ሩሲያ ጥልቅ ግዛት ገብቶ አደጋ በመፍጠርም ስሙ እየተነሳ ይገኛል።
የኪዬቭ ከተማ የደህንነት ባለሞያዎች ፍትህ ለማስፈን እና ገዳዩን ለመያዝ ርብርብ ላይ መሆናቸውም ታውቋል።
