በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከተፈቀደላቸው የቪዛ ጊዜ በላይ መቆየት ከፍተኛ ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ ዜጎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳሰበ።
የኢትዮጵያን ቪዛ አግኝተው የሚመጡ የሌላ ሀገር ዜጎችም ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ መቆየት በሀገሪቱ ህግ መሰረት ቅጣት የሚያሰጥ መሆኑንም ተገልጿል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የሚኒስቴሩን የበጀት ዓመት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በወቅታዊ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
አምባሳደሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአሜሪካ መንግስት የቪዛና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በሚመለከት አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አስታውሰው፤ ለዜጎች ከዚህ አኳያ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ከኢትዮጵያ ወደአሜሪካ የሚደረጉ ጉዞዎች በተማሪነትም ሆነ በቱሪስት ቪዛ ከተፈቀደላቸው የቪዛ ጊዜ በላይ መቆየት ከፍተኛ ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ወደፍትም ለትምህርትም ሆነ ለጉብኝት የመጓዝ እድል ያላቸው ዜጎች የተቀመጠውን የቪዛ ቆይታ ጊዜ ካላከበሩ ለችግሮች ልዳረጉ ስለሚችሉ ከወዲሁ እንዲጠነቀቁ አስገንዝበዋል።
ኢንዲሁም ወደአሜሪካ ለመጓዝና ቪዛ ለማግኘት ወደኤምባሲ የሚሄዱ ግለሰቦች ከመንግስትም ሆነ ከዬትኛውም ከግል ተቋማት የሚመነጩ ሰነዶች ትክክል ስለመሆናቸውና በቃለመጠይቁ ወቅት የሚሰጡ መረጃዎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
በሌላ በኩል ከአሜሪካም ወደኢትዮጵያ ጉዞ የሚያደርጉ የአሜሪካ ፓስፖርት የያዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንም ሆኑ የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች የኢትዮጵያ ቪዛ አግኝተው ሲመጡ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ መቆየት በሀገሪቱ ህግ መሰረት ቅጣት የሚያሰጥ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ይህ አሰራር የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ያልያዙትን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እንደሚያካትት አምባሳደሩ ተናግረዋል።
