የግሉ ዘርፍ ተወዳዳሪነት እንዲጎለብት የተጠናከሩ የቢዝነስ ትንታኔዎች እንደሚያስፈልጉ አዲስ ቻምበር ገለፀ

Date:

የሚዲያ ተቋማት ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ ንግድ ምክር ቤቱ እውቅና እና ምስጋና አቅርቧል፡፡

አዲስ ቻምበር አመታዊ የቻምበር ሚዲያ ቀንን ከብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ጋር በመሆን አከብሯል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ የግሉን ዘርፍ በማጠናከር በሀገሪቱ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የበኩሉን ሚና እያበረከተ መሆኑን የምክር ቤቱ ዋና ጸኃፊ ዶ/ር መሰረት ሞላ ለታዳሚው ተናግረዋል፡፡

የንግድ ምክር ቤቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ከሚዲያ ተቋማት ጋር በመተባበር በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ለተሰማራው ህብረተሰብም ሆነ ወደፊት ለሚመጡ ስራ ፈጣሪዎች ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ በማቅረብ የኢትዮጰያ ኢኮኖሚን መደገፍ ነው ብለዋል።

በተለይ መረጃና ሚዲያ የኢኮኖሚ ልማት ሀሳብ መቀመሪያ፣መጠንሰሻ እና ማስተጋቢያ መድረክ መሆኑን በመረዳት ንግድና ኢንቨስትመንት አለም አቀፋዊ ገጽታ ተላብሶ ንግድ ድርጅቶችም ሆኑ አገሮች በከፍተኛ የውድድር ትንቅንቅ ውስጥ በገቡበት በአሁኑ ወቅት የሀገራችን ነጋዴዎች ለሀገር ውስጥም ሆነ ለአለም አቀፍ ገበያ የሚያቀርቧቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ተወዳዳሪነት እንዲያጎለብቱ የተጠናከረ የቢዝነስ ትንታኔዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡ ፡

የሚዲያ ባለሙያዎችም ይህን በመገንዘብ ሀገራዊ ሀላፊነታችሁን እንዲወጡ ያሳሰቡ ሲሆን ንግድ ምክር ቤቱ 78ተኛ አመቱን ማስቆጠሩን አውሰተው የቻምበሩን ስራዎች ለማስተዋወቅ  ከመንግስትና የግል ሚዲያዎች ጋር  አብረን መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ይህ ቀን በተለይም  ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ለሚያደርገው አስተዋጽኦ ሚዲያዎች ከጎኑ በመሆን ላደረጉት ትብብርና የሚዲያ ድጋፍ እውቅና እና ምስጋና አቅርቧል፡፡

ቀኑን በማስመልከትም በቢዝነስ እና በኢንቫይሮንመንት ዘገባ ዙሪያ የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡ ፡

በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዙሪያ የመነሻ ጽሁፋቸውን ያቀረቡት ተመራማሪውና ሳይንቲስቱ ዶ/ር ታደሰ ዳባ ሲሆኑ በቢዝነስ ዘገባ ዙሪያ የካፒታል ጋዜጣ ም/ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሙሉቀን የወንደሰን እና በአዲስ ቻምበር የአድቮኬሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር በአቶ ካሳሁን ማሞ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል  ::

የቻምበር ሚዲያ ቀን እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደረጉ አጋር አካላትና ባለሙያዎች ከአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ እጅ የእውቅና ሰርቲፊኬት ተቀብለዋል፡ ፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...