
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን ህዝቡ እንዲመርጥ የሰጡት እድል ለዲሞክራሲ የቀረበ ቢሆንም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አማካሪ ምክር ቤቱን ያገለለ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ለሃገሬ ቴሌቪዥን ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡
የትግራይ ነጻነት ፓርቲ የጽህፈት ቤት ሃላፊ ጣዕመ ሃጎስ፣ የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን ህዝቡ በኢሜይል እንዲመርጥ መጠየቃቸው ሌሎች ከክልሉ ውጪ ያሉ አካላትም እንዲመርጡ የሚያደርግ በመሆኑ ስህተት እንደሆነ አንስተዋል፡፡
አካሄዱ የተለያዩ የትግራይ ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት የተካተቱበትን የጊዜያዊ አማካሪ ምክር ቤቱን ያገለለ ነው ሲሉም ወቅሰዋል፡፡
ህውሃት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተግባር የፕሪቶርያውን ስምምነት የጣሰ ነው ማለቱ የሚታወስ ሲሆን በጠመንጃ ታግዞ መፈንቅለ ግዝያዊ አስተዳደር ያደረገው ህወሃት የፕሪቶሪያው ስምምነት ተጣሰ ማለቱ ውሃ የማያነሳ ጉዳይ ነው ሲሉ አቶ ጣዕመ ተችተዋል፡፡
ሌላው አስተያየታቸውን ለጣቢያችን የሰጡት የትግራይ ባይቶና ፓርቲ ሊቀመንበር ክብሮም በርሄ በበኩላቸው፣ ሁለቱም ወገኖች የፈጸሙት ድርጊት ህግን የተከተለ አይደለም ብለዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያገለለ እና ያላማከረ መሆኑ አግባብነት የለውም ሲሉም አቶ በርሄ አክለው ተናግረዋል፡፡
ሀገሬ ቲቪ