ኦርቶዶክስ ቀጥተኛዋ መንገድ ናት! /Hope Church Halifax/
በእንግሊዝ ሀገር የሚገኝና የፕሮቴስታንት እምነት አካል የሆነ Hope Church Halifax የተባለ ቤተክርስትያን ከነ-ተከታዮቹ ጠቅልሎ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን መቀበሉ የድንግል ማርያምና የፃድቃንን አማላጅነት እንደሚቀበል ይፋ አድርጓል ።
ቤተእምነቱ hopehalifax.org/orthodoxy በድህረ ገፁ በኩል እንዳሳወቀዉ ከሆነ ለአምስት ዓመታት ሁሉ ስለ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሲያጠና እንደነበርና አሁን በይፋ የአንፆኪያ ኦርቶዶክስ (ግሪክ) ቤተክርስቲያንን መሰረተ እምነት መቀበሉን አውጇል።
በዚህ አቋሙም አንዳንዶች ሊገረሙ እንደሚችሉ ሲጠቅስ እውነታውን ግን ብርሃንን በምልዓት ወደ ማየት ተሸጋግረናልና ኑና እኛ የቀመስነውን እውነት ቀምሳችሁ እዩ በማለት ለሌሎችም ጥሪውን አቅርቧል። አያይዞም:- ውይይት የሚፈልግን ማንኛውንም አካል:- አቅራቢያው ወደሚገኙ የኦርቶዶክስ አጥቢያዎች ሄደው እንዲማሩ እንዲሁም የእነርሱን መርሃ-ግብራት እንዲለታተሉ ጋብዟል። በረጅም ጊዜ በጥንቃቄ መጻሕፍትን መርምረን ያገኘነውን ብርሃን ኑና እዩ ብሎ ጥሪ አቅርቧል።
ምንጭ hopehalifax.org/orthodoxy
የኔታ ቲዩብ
የፕሮቴስታንት ሙሉ ቸርች ኦርቶዶክስን ተቀበለ !
Date:
