የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ

Date:


          
በአገር አቀፍ ደረጃ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና መጠናቀቁን ተገልጿል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ.ም በመላ አገሪቱ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ከዝግጅት ጀምሮ በፈተናው ወቅት በየደረጃው የሚገኙ በፈተናው ስራ የተሳተፉ ባለሙያዎች ፣ አመራሮችና ባለድርሻዎች በፈተናው ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ፈተናው በሰላም ተጠናቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የፈተናው ስራ እንዲሳካ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለተወጡ ኃላፊዎች፣ አስተባባሪዎች፣ ፈታኞች፣ የጸጥታ አስከባሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻዎች ላበረከቱት አስዋጽኦ ምስጋና ያቀርባል፡፡

ተፈታኞችም ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ላሳዩት በጎ ስነ ምግባር አያመሰገነ መልካም እድል እንዲገጥማቸው ትምህርት ሚኒስቴር ምኞቱን ይገልጻል፡፡

የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ(12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ በወረቀትና በበይነ መረብ በመላ ሀገሪቱ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...