ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ5.1% ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
ዳሸን ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት አመት የ31.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገቡንም ባንኩ በዛሬው እለት ባካሄደው ጠቅላላ የባለአክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ይፋ አድርጓል።
ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ34% ከፍተኛ ጭማሪ የታየበት መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ጠቅላላ ሃብቱን ከ254 ቢሊዮን ብር በላይ መሻገሩን የገለፀም ሲሆን፣ ይህም በቀደመው የበጀት ዓመት ከነበረው 183.7 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ38.5 በመቶ ዕድገት የተመዘገበበት መሆኑንም ገልፃል።
የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠንም 202.2 ቢሊዮን ብር መድረሱ ሲገለፅ ፣ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ38.7% ጉልህ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
ከጠቅላላው የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ የዳሸን ባንክ ወለድ ነፃ አገልግሎት (ሸሪክ) የ15.8 ቢሊዮን ብር አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ42.3% ከፍተኛ ዕድገት የታየበት እንደሆነም ተነስቷል።
ባንኩ በውጭ ምንዛሪ ግኝት ረገድም ከፍተኛ አፈፃፀም መመዝገቡንም ገልፆ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ15.58% ጭማሪ ያለው 1.12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል ብሏል።
የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን ጨምሮ የባንኩ አጠቃላይ የብድር ክምችት መጠን በሂሳብ ዓመቱ መጨረሻ 134 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲመሳከር የ17.3% ዕድገት ታይቶበታል፡፡
በሌላ በኩል የባንኩ ካፒታል ባለፈው የበጀት ዓመት መጨረሻ የ2.3 ቢሊዮን ብር ዕድገት በማሳየት 14.3 ቢሊዮን ብር መድረሱ በእለቱ ተጠቅሷል።
ዳሸን ባንከ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመትም የደንበኞቹን ቁጥር በ17.4% በማሳደግ በጠቅላላው 7.88 ሚሊዮን አድርሻለሁ ያለ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የቅርንጫፎቹን ቁጥር በዓመቱ መጨረሻ 906 ማድረስ መቻሉን አስታውቋል።
ባንኩ የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን ለመወጣት በበበጀት ዓመቱ ለማህበረሰብ ተኮር ስራዎች እንዲሁም ለአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራሞች በድምሩ 108.6 ሚሊዮን ብር ፈሰስ ማድረግ መቻሉንም ገልፃል።
