የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስ በአስቸኳይ ትጥቅ ካልፈታ “ገሃነም ይወርድበታል” ሲሉ አስጠነቀቁ።
ትራምፕ ይህንን የዛቻ ንግግር የተናገሩት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በፍሎሪዳ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ሲሆን ለኔታንያሁ ያላቸውን የማይናወጥ ድጋፍም በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ትራምፕ በጋራ በሰጡት መግለጫ ሃማስ
ትጥቁን እንዲያስረክብ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህ ካልሆነ ግን ቡድኑ ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ሃማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ከመፍታቱ በፊት እስራኤል ወታደሮቿን ስለማስወጣቷ መወያየታቸውን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ “በተስማሙት መሠረት ትጥቅ ካልፈቱ ሀማስ ከባድ ነገር እንደሚጠብቀው ተናገረዋል። “እኛ ያ እንዲሆን አንፈልግም ፍላጎታችንም አይደለም ፣ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትጥቅ መፍታት አለባቸው” ሲሉ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሲቪል ክብር ሽልማት የሆነውን “የእስራኤል ሽልማት” (Israel Prize) እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
ይህ ሽልማት እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ ከተመሰረተ ጀምሮ እስካሁን ድረስ እስራኤላዊ ላልሆነ ሰው ተሰጥቶ የማያውቅ ሲሆን ትራምፕ ይህንን ሽልማት የሚያገኙ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ዜጋ ይሆናሉ ተብሏል።
ዘገባው የ ዘ ጋርዲያን ነው
