ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ260 ሺህ ዶላር የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ አደረገች

Date:

የጣሊያን መንግሥት በኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ግንባታን ለማገዝ እና የድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎትን ለማጠናከር ከ260 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚገመት የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ድጋፍ አድርጓል።

የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶቹን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ የተረከቡ ሲሆን፣ ልገሳው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ወዳጅነት የሚያሳይና ኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም መሣሪያዎቹ በሆስፒታሎች የሚሰጠውን ምርመራ የማድረግና ሕይወት የማዳን ተግባር ይበልጥ እንደሚያጠናክሩት አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን በአጭር ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር መቻሏን አድንቀው፣ ድጋፉ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።

የልገሳ ሥነ ሥርዓቱ የሁለቱን አገራት የቆየ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱቃድር ገልገሎ ናቸው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...