ፕሬዜዳንት ጌታቸው ” ኋላቀር ቡድን ” ለምን አሉ ?

Date:

ከትግራይ ክልል ” ለስራ ” በሚል ምክንያት ከወጡ 20 ቀናት ያስቆጠሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን ለህክምና አንዴ ወደ ዱባይ ሌላ ጊዜ ወደ ባንኮክ ተጉዘዋል እየተባለ ሲነገርባቸው ነበር።

ትላንት እሁድ በሰዓታት ልዩነት ሁለት መልእክቶችን አጋርተዋል።

አንዱ ለህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የሚል ሲሆን ፤ ሌላኛው ለተቀናቃኞቻቸው ” ድሉ የህዝብ ነው ” የሚል ጠንካራ ትችት አዘል መልእክት ነው።

” ላለፉት 20 ቀናት በትግራይ እየታየ ያለው ፓለቲካዊ ቀውስ ‘ ስልጣን ወይ ሞት ‘ የሚል ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት የደሎተው ሴራ መጨረሻው ምዕራፍ ማሳያ ነው ” ብለዋል።

ይህ ደሞ አንዳንድ የተሻለ ስምና ዝና ያላቸውን ግለሰቦችም ለስህተት የዳረገ ፍፃሜ ነው በማለት ተግባሩ አጣጥለውታል።

ፕሬዜዳንቱ ” ኋላቀር ቡድን ” ሲሉ የገለፁት አካል የጊዚያዊ መንግስቱ መዋቅር በመጣስ ማህተም ከተቆጣጠረ በኋላ በመጀመሪያ እርምጃው በትላለቅ ከተሞች ለደጋፊዎቹ በስፋት መሬት አከፋፍሏል ፤ ገቢ የሚያስገኙለትን የሽያጭ ስራዎች ፈፅሟል ብለዋል።

” መሬት ከመሸጥና ከማከፋፈል አልፎ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው መመለስና ግዛታዊ አንድነት ማረጋገጥ ከመፈክር በዘለለ ጣጣው አይደለም ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ኋላቀር ቡድን ” ሲሉ የገለፁት አካል ሁለተኛ ትኩረቱ ወደ
#ፌደራል እየተመላለሰ የፕሬዜዳንት ስልጣን እንዲሰጠው መለመን ሆኗል ሲሉ አብራርተዋል።  

” ቡድኑና አሽከሮቹ በህልምና በቀልባቸው የማይለቁዋቸው ሁለት አጀንዳዎች መሬትና ስልጣን ናቸው ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ቡድኑ የሚያስተባብራቸው አካላት የተፈናቃዩ ተስፋና የወጣቱን ህልም በመቀማት ወደ ሁለተኛ ዙር ትርምስ ሊከቱን ታችና ላይ በማለት ስለሚገኙ ህዝቡ ሃይ ሊላቸው ይገባል ” ሲሉ አክለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩትን ጠንከር ያለ ፅሁፍ ” ድል የህዝባችን ነው ” ሲሉ ቋጭተውታል።

#TikvahEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...