ሁለት ባንኮች በኢትዮጵያ የመጀመርያው የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኙ

Date:



ሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ኢንቨስትመንት ባንክ እና ወጋገን ካፒታል አክሲዮን ማህበር ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ያገኙት የመጀመርያው የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው።

እነዚህ ባንኮች እራሳቸውን ችለው የተቋቋሙ የካፒታል ገበያ ስራ ብቻ የሚሰሩ የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው።

በተጨማሪም ለአምስት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ ተሰጥቷል።

ፈቃድ የተሰጣቸው አገልግሎት ሰጪዎች ህጉ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶችና መመዘኛዎች አሟልተዋል ተብሏል።

ይህንን ፈቃድ አስመልክቶ ዛሬ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ቦርድ ሰብሳቢ ማሞ ምህረቱ አብስረዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገበያው  የሀገሪቱን የክፍያ ሚዛን ያረጋጋል ከውጭ ብድር ጥገኝነትና የውጭ ብድር በመቀነስ የማክሮ ኢኮኖሚ ማረጋጋትን ይፈጥራል ብለዋል።

ታማኝነት ያለው የፋይናነስ ሥርዓት ለመገንባት የተዘረጋው የካፒታል ገበያ፤ ለማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል።

ገበያው አዲስ እንደመሆኑ መጠን ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ከሚመለከታቸው ጋር አብሮ ለመስራት እድል መፈጠሩ ተነግሯል።

የኢንቨስትመንት ባንኮችና የሰነደ ሙአለ ነዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪዎችን  ጨምሮ ዛሬ ፈቃድ ያገኙ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች በድምሩ ዘጠኝ ደርሰዋል።

የኢትዮዽያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ ዛሬ ፈቃድ የተሰጣችሁ በሙሉ ስራችሁ ሀላፊነት የተጣለበት በመሆኑ ህጉን አክብራችሁ እንድትሰሩ ሲሉ አሳስበዋል።

እነዚህ የኢንቨስትመንት ባንኮች ከንግድ ባንኮች የሚለዩ ሲሆን ቁጠባን አያሰባስቡም፤ ብድር አይሰጡም።

በምትኩ ኢንቨስትመንትን በማማከር በሌሎች የካፒታል ገበያ ስራዎች መሳተፍ እንደሚችሉ ሰምተናል።

ከሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...