ሃማስ የመጨረሻውን አሜሪካዊ ታጋች እንደሚፈታ አስታወቀ

Date:

ቡድኑ የመጨረሻውን የተኩስ አቁም ስምምነት እና የእስረኞች መለዋወጥ ላይ ያተኮረ አፋጣኝ እና ጥልቅ ድርድር ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑንም ገልጿል።

ሃማስ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚደረገው ጥረት እስራኤላዊ-አሜሪካዊ ታጋች ኢዳን አሌክሳንደርን እንደሚፈታ አስታውቋል።

ሃማስ እንደተናገረው የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማስፈን ሸምጋዮች ባደረጉት ጥረት ቡድኑ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር እየተነጋገረ መሆኑን እና ሁኔታዉም ከፍተኛ አዎንታዊ ምላሽ እንዳለዉ ገልጿል።

በጋዛ ድንበር በእግረኛ ጦር ውስጥ ያገለገለው ወታደር አሌክሳንደር በጋዛ ውስጥ እስካሁን በህይወት ያለው የመጨረሻው የአሜሪካ ታጋች መሆኑ ይታወቃል።

የእሱ መፈታት የተኩስ አቁምን ለማመቻቸት፣ የድንበር ማቋረጫ መንገዶችን ለመክፈት እና የሰብአዊ ርዳታ እና የእርዳታ አቅርቦቶችን ወደ ጋዛ ሰርጥ ለማስገባት እንደ ዕቅድ ከተያዙ በርካታ እርምጃዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሃማስ የመጨረሻ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲሁም የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ እና ጋዛን የሚያስተዳድር ራሱን የቻለ አካል ለማቋቋም ያለመ አፋጣኝ እና ጥልቅ ድርድር ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑንም ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...