ለትግራይ አዲስ ፓርቲ ሊቋቋም ነዉ

Date:

የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ፣ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ፓርቲ ለመኾን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል። ቡድኑ ወደ አንድ ፓርቲነት ለመቀየር የወሰነው፣ ለትግራይ የወደፊት ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ዕጣ ፋንታ ለመታገል እንደኾነ ገልጧል።

ቡድኑ፣ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ በጊዜያዊ አስተዳደሩ እገዛ የማዕድን ዘርፉንና የትግራይ ልማት ማኅበርን ጨምሮ የትግራይ ቁልፍ ተቋማትን በብቸኝነት በመቆጣጠር ላይ ይገኛል ብሏል።

ሲቪል ማኅበራት ድርጊቱን ለማስቆም በፍርድ ቤት ጭምር እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ የጠየቀው ቡድኑ፣ የደብረጺዮን ቡድን ቁልፍ ተቋማትን እንዲቆጣጠር ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለቡድኑ ይሠጠዋል ያለውን ድጋፍ እንዲያቆምም ጠይቋል። የጌታቸው ቡድን ይህን እንቅስቃሴ መጀመሩ የተሠማው፣ ምርጫ ቦርድ የሕወሓትን ሕጋዊነት እሠርዛለሁ ያለበት ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት በቀረው ሰዓት ላይ ነው።

[ዋዜማ]

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...