ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሶስት ቀናት የሚቆይ  የዳሌና ጉልበት መገጣጠሚያ  ንቅለ ተለካ እየሰጠ ይገኛል

Date:

ላለፉት አስራ ሰባት አመታት የተለያዩ ሕከምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ላንድማርክ  አጠቃላይ ሆስፒታል በሕንድ ሀገር ከሚገኘው ፎርቲስ ከተባለ ሆስፒታል ጋር በመተባባር ከሐምሌ 21 እስከ 23 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ህክምና እየሰጠ መሆኑን አስታዉቋል።

የዳሌና ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ንቅለ ተለካ ህክምናው የሚሰጠው  ከህንድ  ሀገር ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች በማስመጣት እንደሚሰጥ ተገልፆል፡፡

ሆስፒታሉ ከፎርቲስ ሆስፒታል ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር  የፎርቲስ ሆስፒታል ተወካይ ቢሮ መከፈቱ ተነግሯል፡፡ የንቅለ ተከላው አገልግሎት የሚሰጠው ለሦስተኛ ዙር መሆኑን የተነገረ ሲሆን የሚመጡ ታካሚዎች እንደየ ወረፋቸው የሚስተናገዱ እና ዋጋው ተመጣጣኝ ነው ሲሉ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ፕሮፌሰር ከበደ ወሌአያና  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቀዶ ህክምናው በሦስት ዶክተሮች እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የሀኪሞችን ቁጥር በመጨመር የህክምና አገልግሎቱ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

የዳሌና የጉልበት መገጣጣሚያ ሕመም መንስኤው በርካታ ሲሆን በተለይም ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የመገጣጠሚያ መሸርሸርና መሰባበር እንዲሁም ታካሚዎች ለሌላ ሕመም በሚወስዷቸው መድሃኒቶች ምክንያት እንዲሁም በአካል ክፍሎቹ ላይ ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ እንደሚያጋጥም ተገልጿል፡፡

በሆስቲታሉ በየዓመቱ ከ 30 እስከ 40ሺ ለሚሆኑ ታካሚዎች የተለያየ የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልፆል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...