ሕብረት ባንክ በተጠናቀቀው 2018 በጀት አመት 5.46 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ተናገረ
ትርፉ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲመሳከር የ 4.71 ቢሊየን ብር ጭማሪ አሳይቷል።
የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብም 124 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግሯል።
ህብረት ባንክ ይህን ያለው ዛሬ በሸራተን ሆቴል ባካሄደው 29ኛ መደበኛ እና 15ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው።
ባንኩ ጠቅላላ የብድር መጠኑ 20.17 ቢሊየን ብር አመታዊ እድገት አሳይቶ ከወለድ ነጻ የብድር አገልግሎትን ጨምሮ በአጠቃላይ የሰጠው ብድር 99.49 ቢሊየን ብር ደርሷል ብሏል።
የባንኩን የበጀት አመት ሪፖርት ያቀረቡት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው አቶ መስፍን ተሰማ በሂሳብ አመቱ መዝጊያ የባንኩ ጠቅላላ የሀብት መጠን የ36.70 ቢሊየን ብር አመታዊ እድገት በማስመዝገብ 150.63 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 16.95 ቢሊየን ብር መድረሱንና ይህም ካለፈው የሂሳብ አመት የ4.66 ቢሊየን ብር እድገት አስመዝግቧል ተብሏል።
ህብረት ባንክ በተጠናቀቀው 2018 በጀት አመት 433.3 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማስመዝገቡንና ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ133.24 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት በኩልም በከወንኳቸው ስራዎች በአጠቃላይ በሂሳብ አመቱ 46.7 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሰጥቻለሁ ብሏል።
