ማይክ አርቴታ ከደርቢው ጨዋታ አንድ ነጥብ ለመጋራት ብሪጅ የደረሰ መሰለ ። ከ55 ደቂቃዎች በላይ የነበረውን የተጨዋች ብልጫ አድቫንቴጅ ተከትሎ የተፈጠረለትን ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ አጋጣሚ አመከነ ።
የመድፉ አለቃ ማይክ አርቴታ ከቼልሲ ኋይል የቀላቀለ የጨዋታ ስትራቴጂ ጋር እንደተመሰጠም ፈፀመ ። አርሰናል ከቼልሲ 10 ኮኮቦች ፊት የነበረው የተቀዛቀዘ የማጥቃት እንቅስቃሴ የጨዋታ ሜንታሊቲና ፍላጎት ብዙዎችን እንዳነገጋረ ለንደን ደርቢን በአቻ ውጤት ፈፅሟል ።
ከዋና ኮኮቡ ካይሲዶ ቀይ ካርድ በኋላ ሚስተር ቼልሲ በጨዋታው ይቸገራል ሲባል ጭራሽ አንሰራራ ። ከቀይ ካርዱ በኋላ የማሬስካ የጨዋታ ቀመር ከመድፉ ፊት የተሳካ ሆነ ። ከዕረፍት መልስ ቼልሲ 1ለዐ በቻሎባ ጎል ቀድሞም መራ ።
ከአምበሉ ኦዴጋርድ ቅያሪ ተፅእኖ ጋር አርሰናል 1ለ0 የተመራውን ጨዋታ ወደ አንድ አቻ ውጤት በሜሬኖ ጎል በብርሃን ፍጥነት ቀየረ ። መድፉ የአቻዋን ጎል ተከትሎ በዛው የጀመረውን የማጥቃት ቴምፖ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲባል ግን መልሶ በጨዋታው ከማሬስካ ተደናቂ ጨዋታን የማስተዳደር ታክቲካል ማስተር Class አቅም ጋር ደበዘዘ ። የቼልሲ ኮኮቦች ውጤቱን ይዞ ለመውጣት የነበራቸው የተሳካ የደርቢው ፍጥጫ Dark Art እንቅስቃሴ ውስጥ አርሰናል እንደተመሰጠ ቀረ ።
ከጨዋታው ጅማሮ አንስቶ በፀብ አጫሪ ኋይል የቀላቀለ የጨዋታ እንቅስቃሴ ዝግጁነት መድፈኛውን በደርቢው ቀን በብሪጅ ያስተናገደው ቼልሲ የገጠመውን የካይሲዶ ቀይ ካርድ ተከትሎ በ10 ተጨዋች ሳይቸገር የተሻለም ተንቀሳቅሶ መደፈኛውን አፈዘዘ ።
ቼልሲ አርሰናል የሲዝኑ ውጤታማ አጀማመሩን ተከትሎ በአድናቆት ቃላት አጀብ ብቻ የቆየው የሊጉ መሪ መድፈኞች እስካሁን ያልታዩ ሰፊ የቡድን ክፍተቶችን አንፀባረቀ ። አርሰናል ያለ ዋና ዋና የተከላካይ መስመር ደጀኖቹ ሳሊባ እና ማጋሊሽ ወትሮም እንደተጠበቀው ተቸገረ ።
በዴክላን ራይስ ሕያው አስደናቂ ተጋድሎ ሰፊ ከላላ ተደርጎላቸውም ከቼልሲ የማጥቃት እንቅስቃሴ ፊት የሳሊባ እና ማጋሊሽ አልጋወራሾች ሲወከቡ አመሹ ። ግብ ጠባቂው ዴቪድ ሬያም ያለ ሳሊባ እና ማጋሊሽ ያለ ስራ እንደተቀመጠ 90 ደቂቃውን የመጨረስ ሰሞናዊ ልምድ ፉርሽ ሆነ ።
ለላፉት 162 ቀናት ፀንቶ የዘለቀው የሳሊባ እና ማጋሊሽ ተደናቂ የመድፉ ኮንክሪት ጥምረትን በአንድ ጀምበር ሄንካፔ እና ማስኬራ ሊወርሱ እንደማይችሉም ታየ ። ጠንቃቃው አርቴታም ከቼልሲ ኋይል የቀላቀለ የጨዋታ ስትራቴጂ ጋር እንደተመሰጠ የሞየስስ ካይሲዶ ቀይ ካርድን ተከትሎ በደርቢው ቀን የተፈጠረለት ጨዋታውን የመቆጣጠር የማሸነፍ አጥቅቶ የመጫወት ሶስት ነጥብ ይዞ የመውጣት ዕድሉን አምክኖ ከምዕራብ ለንደን አንድ ነጥብ ይዞ ተመልሷል ።
ሚስተር ቼልሲ በ10 ተጨዋች ዋና የከተማ ባላንጣው አርሰናልን እንዳፈዘዘ ነጥብ ተጋርቶ ደርቢውን ፈፅሟል ። ጨዋታው የአርሰናል ደካማው የሲዝኑ አቋም ሆኗል ። 20 ዓመት ለተሻገረው የመድፉ የዋንጫ የተናፈቀ ህልም አርሰናል ከተራራው የስኬት ጫፍ ለመድረስ በገናናው ሊግ ኋያል የፉክክር ማዕበል ገና በአስደናቂ የቡድን መዋቅሩ ውስጥም አርሰናል በፈተናው እንደሚቀጥል የዛሬው የቼልሲ የለንደን ደርቢ ጨዋታ ማረጋገጫውን ሰጥቷል ።
በsuper sunday የሊጉ ሌሎች ጨዋታዎች የዩናይትድ ሄድ መለስ ቀጥሏል ። ከኤቨርተን ደካማ አቋም ማግስት ዩናይትድ ወደ ደቢብ ለንደን አቅንቶ ፓላስን 2ለ1 ረቷል ። ጨዋታውን በድል በመፈፀም ውስጥ ከሚገኝ ጠቀሜታ ባሻገር የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የጨዋታ ቀመርና የዩናይትድ ተጨዋቾች እንቅስቃሴ ዛሬም በትልቅ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንደወደቀ ጨዋታው ተጠናቋል ።
ከተደራራቢ ሽንፈት የውጤት ቀውስ ጋር በተያያዘ ጨንቆት የከረመው ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ዌስትሃምን 2ለ0 ረቶ መጠነኛ ዕፎይታ አግኝቷል ። 130 ሚሊዮን ፓውንድ ያስወጣው አሌክሳንደር ኢሳክም የመጀመሪያውን ጎሉን በሊጉ አስቆጥሯል ። አሰልጣኝ አርን ስሎት ከኤልዛቤት ፓርክ የቀዩ ምድር ዋና ኮኮብ ሞሃመድ ሳላህን ሙሉ የጨዋታ ጊዜ ተጠባባቂ ወንበር ላይ እንዳስቀመጡ የራቀቸውን ድል መዶሻው ዌስትሃም ላይ አስመዝግበዋል
Tribune sport
