አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞችም ቢሮ በመክፈት የአርበኞቹን ታሪክ በማደራጀት የተለያዩ ታሪካዊ ሰነዶችን የማሰባሰብ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ለአሐዱ ገልጿል።
የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ የአርበኞችን ቀን ከማክበር ባለፈ የአርበኞችን ታሪክ ሰንዶ ማስቀመጥ የታሪክ ክፍተትን ከመቀነስ አንጻር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
የአርበኞቹን ታሪክ ከማሰባሰብ በተጨማሪም፤ አሁን ላይ በሕይወት ያሉ አርበኞችን የመደገፍ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ታሪክ አሰባስቦ የመሰነዱን ሥራ ለማከናወን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እየተደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው፤ የተደራጀ ሥራ ለመስራት የበጀት እጥረት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
