ማንችስተር ዩናይትድ ተከታታይ ድል አስመዘገበ

Date:




በ24ተኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐግብሮች ማንችስተር ዩናይትድ ድል ሲቀናው ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ።

ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሀምን 3ለ2 ማሸነፍ ችሏል።

የቀያዮቹ ሰይጣኖችን የማሸነፊያ ግቦች ማቲውስ ኩንያ ፤ ካሲሚሮ እና ቤንጃሚን ሴስኮ አስቆጥረዋል።

ፉልሀምን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ኬቪን ሳንቶሰ እና ራኦል ሂምኔዝ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ሶስተኛ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን አሳክቷል።

ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የማንችስተር ሲቲን ግቦች ረያን ሼርኪ እና አንቶይን ሴሜኒዮ ሲያስቆጥሩ ዶሚንክ ሶላንኬ ሁለቱንም ግቦች በማሰቆጠር ቶተንሀምን አቻ አድርጓል።

ቶተንሀም ያለፉትን ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ማንችስተር ሲቲ ካለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ነው።

በሌሎች የትላንት ጨዋታዎች

– ብሬንትፎርድ አስቶን ቪላን 1ለ0 ሲያሸንፍ
ክሪስታል ፓላስ ከኖቲንግሃም ፎረስት 1ለ1 ተለያይተዋል

በ24ተኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻው መርሐግብር ዛሬ ሲደረግ ምሸት 05:00 ሰንደርላንድ በሜዳው ሰታዲየም ኦፍ ላይት ላይ ከ በርንሌይ ጋር ይፋለማሉ።

የሊጉ ደረጃ

1. አርሰናል   :- 53 ነጥብ
2.ማንችሰትር ሲቲ  :- 47 ነጥብ
3. አሰቶን ቪላ  :- 46 ነጥብ
4.ማንችሰትር ዩናይትድ :- 41 ነጥብ
5. ቼልሲ  :- 40 ነጥብ
6.ሊቨርፑል :- 39 ነጥብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...