የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማንኛዉም በዉልና ኢንቨስትመንት እርሻ የለማ ምርት ግብይት የሚፈፀምባቸዉ ምርቶች ከታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የክፍያ ርክክብያቸዉ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ብቻ እንዲሆን ወስኗል።
ይህንን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን በውሳኔው ላይ አስመራቾች/ላኪ ድርጅቶች ላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ በሰጠበት ደብዳቤ ላይ ነው።
ምርት ገበያ ባለሥልጣኑ ከውሳኔው በኋላ አስመራቾች/ላኪ ድርጅቶች “ክፍያውን ቀድመን ላመረተልን አካል ክፍያ ስለፈፀምን በድጋሚ ክፍያ ለመፈፀም ተቸግረናል” የሚል ቅሬታ ማቅረባቸውን ጠቅሷል።
ቅሬታቸውን በመቀበል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከምርት ገበያው ጋር ጥናት በማስጠናት ውሳኔ ማስተላለፉን ደብዳቤው ያትታል።
የተላለፉት ውሳኔዎች ምንድናቸው ?
• አስመራቾች/ላኪ ድርጅቶች ከታህሳስ 1 በፊት ላመረተላቸው አካል ክፍያ የፈጸሙበትን የሚያረጋግጥ ሰነድ እንዲያቀርቡ (ህጋዊ የባንክ ማረጋገጫ ደብዳቤ እና የባንክ ማስቀመጫ ደረሰኝ (Deposit slip)።
• ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ወጪ ንግድና ፕሮሞሽን ክፍል የክፍያውን ትክክለኛነት ከባንኮች ጋር በማረጋገጥ ወደ ውጭ የመላክ ፈቃዶችን እንዲሰጥ፡፡
• ከታህሳስ 1 እስከ 16 ድረስ አስመራቾች/ላኪ ድርጅቶች ላመረተላቸው አካል የከፈሉበትን የሚያረጋግጥ ሰነድ ለምርት ገበያው እንዲያቀርቡ (ህጋዊ የባንክ ማረጋገጫ ደብዳቤ እና የባንክ ማስቀመጫ ደረሰኝ/Deposit slip)።
• ምርት ገበያውም በቀረበለት ሰነድ መሰረት ትክክለኛነቱን ከባንኮች ጋር በማረጋገጥ፤ የተቀመጠውን አገልግሎት ክፍያ (0.2%) እና የመንግስትን ታክስ በመሰብሰብ የገንዘብ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጥ (Net obligation report)።
• የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ወጪ ንግድና ፕሮሞሽን ክፍል በዚህ መነሻነት አስመራቾች/ላኪ ድርጅቶች ከምርት ገበያው የሚዛን ሰርተፊኬትና የገንዘብ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ (Net obligation report) ይዘው ሲቀርቡ ወደ ውጭ የመላክ ፈቃዶችን እንዲሰጥ፡፡
• አስመራቾች/ላኪ ድርጅቶች ከታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አዲስ ለከፈሉትና ወደ ፊት ለሚከፍሉት ክፍያ በተቀመጠው አሰራር መሰረት ሙሉ በሙሉ በምርት ገበያው የክፍያ ስርዓት መሰረት ክፍያቸዉ እንዲከፍሉ።
• አስመራቾች/ላኪ ድርጅቶች የከፈሉበትን የገንዘብ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ (Net obligation report) እንዲሁም የሚዛን ሰርተፊኬት በመያዝ በንድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ተወስኗል።
@tikvahethiopia
