ካማላ ሃሪስ በቬንዙዌላ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የትራምፕ ድርጊት ሕገ-ወጥ እና ግድየለሽነት የተሞላበት ነው

Date:

​የቀድሞዋ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በቬንዙዌላ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እና የፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን መታሰር በጽኑ አውግዘዋል።

​ሃሪስ በመግለጫቸው ላይ ትራምፕ በቬንዙዌላ ላይ የወሰዱት እርምጃ አሜሪካን ደህንነቷ የተጠበቀ፣ ጠንካራ ወይም ተደራሽ አያደርጋትም ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

​”ማዱሮ ጨካኝ እና ሕገ-ወጥ አምባገነን መሆናቸው፣ የተወሰደው እርምጃ ሕገ-ወጥ እና ግድየለሽነት የተሞላበት መሆኑን አይለውጠውም። ይህንን ድራማ ከዚህ በፊት አይተነዋል።

የመንግሥት ለውጥ ለማምጣት ወይም ነዳጅ ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጦርነቶች እንደ ጥንካሬ ይሸጣሉ፤ ነገር ግን መጨረሻቸው ትርምስ ይሆናል፤ ዋጋውን የሚከፍሉት ደግሞ የአሜሪካ ቤተሰቦች ናቸው” ብለዋል ሃሪስ።

​አክለውም የአሜሪካ ሕዝብ በውሸት መሰላቸቱን ገልጸዋል፦
​”ይህ ስለ ዕፅ ወይም ስለ ዲሞክራሲ አይደለም። ስለ ነዳጅ እና ትራምፕ በቀጣናው እንደ ኃያል መንግሥት ለመታየት ካላቸው ፍላጎት የመነጨ ነው።

ለእነዚህ ነገሮች ግድ ቢላቸው ኖሮ፣ በዕፅ ዝውውር ጥፋተኛ የተባሉትን ምህረት ባላደረጉላቸው ወይም ከማዱሮ ግብረ-አበሮች ጋር ስምምነት ለመፍጠር ሲሉ የቬንዙዌላን ሕጋዊ ተቃዋሚዎች ባላገለሉ ነበር ።

ፕሬዝዳንቱ ወታደሮችን ለአደጋ እያጋለጡ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያባከኑ እና ቀጣናውን እያናጉ ነው፤ ለዚህም ምንም ዓይነት ሕጋዊ ስልጣን፣ የመውጫ ዕቅድ ወይም ለአገር ውስጥ የሚጠቅም ፋይዳ የላቸውም።” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...