ሜሪ ጆይ አረጋውያን እና ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ የ15 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

Date:

ፕሮጀክቱ የሚተገበረው በደብረብረሃን ከተማ ሲሆን 500 ለሚደርሱ ለችግሩ ተጋላጭ ህፃናት፣ ሴቶች ፣ አረጋውያን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

በከተማዋ ከመንግሥት ተቋማት፣ ከማህበረሰቡ ፣ ከዳያስፖራ ኃብት በማሰባሰብ ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ፣ አረጋውያን እና ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ የ15 ሚሊዮን ብር መፈረሙን የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ተናግረዋል።

ከደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር ለዚሁ ሥራ የሚውል የመሬት ርክክብም የተደረገ ሲሆን የህፃናት ሁለገብ አገልግሎት የማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል።

በደብረ ብረሃን ተጋላጭ ህፃናትን ለመደገፍና የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ለማስጀመር ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና ሄዋን ፋውንዴሽን  የውል ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ሔዋን ፋውንዴሽን ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚውል ቤት ለሜሪጆይ ማበርከቱን ሰምቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...