በትራምፕ የውጭ ፖሊሲ እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ቀውስ ሳቢያ ይበልጥ እየተቀራረበ የመጣው የሞስኮ እና የቤጂንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ጠብቋል ነዉ የተባለዉ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤጂንግን ጎብኝተው በወጡ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ ቻይና የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
የትራምፕ የውጭ ፖሊሲ ሊገመት አለመቻል ሞስኮ እና ቤጂንግን ይበልጥ እያቀራረባቸው መሆኑን ተንታኞች ይገልጻሉ።
ይህ የሁለቱ አገራት ጥልቅ አጋርነት የመጣው በዩክሬን ጦርነት እና በኢራን ውጥረት ሳቢያ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በትራንስፖርት መስተጓጎል በተፈጠረው ቀውስ ነው።
ስትራቴጂካዊው የውሃ መስመር አደጋ ላይ በመውደቁ ቻይና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለማግኘት ይበልጥ ወደ ሩሲያ ፊቷን አዙራለች።
ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ሁለቱንም መሪዎች በአንድ ሳምንት ልዩነት ማስተናገዳቸው በአጋጣሚ የተከሰተ እንዳልሆነ የሚናገሩት ተንታኞች፤ ይህም ቤጂንግ በተከፋፈለው የዓለም ሥርዓት ውስጥ ራሷን እንደ ታማኝና ተደማጭነት ያላት ተዋናይ አድርጋ ለማቅረብ የምታደርገውን ስትራቴጂካዊ ጥረት ያሳያል ብለዋል።
