የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ ከኢትዮጵያ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ጋር የበይነመረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት የሞስኮን ድጋፍ አረጋግጠዋል፡፡
“የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት በውይይቱ ተነስቷል። የሩሲያ ወገን የኢትዮጵያን እቅዶች ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍና የቴክኒክና የማማከር ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል” ሲል የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከውይይቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ሬሼትኒኮቭ የሩሲያና ኢትዮጵያ የንግድ ልውውጥ መጠን እያደገ መሄዱንም ጠቁመዋል። እ.ኤ.አ በ2025 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ2.2 ጊዜ ጨምሮ 191.2 ሚሊየን ዶላር ደርሷል ብለዋል።
ሩሲያ በዋናነት ከኢትዮጵያ የቡና ምርት እያስገባች እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
