ዩክሬን ለሶስተኛ ዙር ድርድር አዳዲስ ሁነቶችን መቀበል አለባት ስትል ሩሲያ አስታወቀች፡፡
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ዩክሬን ከጦርነቱ በኋላ የሚከሰቱ እውነታዎችን መረዳት እና መቀበል ይኖርባታል ብለዋል፡፡
የዛሬ ሶስት ዓመት ጦርነቱ ሲጀመር የነበረው እና አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ለውድድር የሚቀርብ ስላልሆነ፤ ዩክሬን ይህንን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባት ሲሉ ፔስኮቭ አክለዋል፡፡
ዩክሬናውያን በሩሲያ የቀረበላቸውን የስምምነት ረቂቅ ሀሳብ በደንብ ማጤን ይጎድላቸዋል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ በሰብአዊነት ጉዳይ ቀደም ሲል የተደረሱ ስምምነቶች ለቀጣይ ውይይቶች መሰረት በመሆናቸው ዩክሬናውያን መቀበል አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በጦርነቱ ብዙዎች ቆስለዋል፤ ወጣቶች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እድል ሰጥተናል፤ ይህ ደግሞ ለቀጣይ ድርድሮች መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ ፔስኮቭ ገልጿል።
በሶስትዮሽ ጉዳዮች ማለትም በፕሬዝዳንት ፑቲን፤ ትራምፕ እና ዘለንስኪ ሊደረጉ የሚገባቸው ነጥቦች አስቀድሞ ዝግጅት እንደተደረገባቸው የክሬምሊን መረጃች አመላክተዋል፡፡
ዘገባው የአናዶሉ ነው
