ላለፏት 18 ወራት በዶኔስክ ግዛት ቻስየቭ ያር ከተማ በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ጦርነት ትላንት በሩሲያውያን የበላይነት ተጠናቋል ።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ጠንካራ የዩክሬን ምሽግ የነበረችውን ቻስየቭ ያርን በቁጥጥር ስር አውሏል ።
ከአመት ቷፊት አንድ የዩክሬን ከፍተኛ የጦር መኮንን እንደተናገሩት ከሆን ይህችንን የጦር ስትራቴጂክ ከተማ ማጣት ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብለው ነበር ።
የሩሲያ ጦር በቀጣይ በዶኔስክ ወደ አሻው ስፍራ ለመገስገስ ወሳኝ ስፍራ ተቆጣጥሯል ተብሏል ።
12,000 በላይ ነዋሪዎች ይኖሩባት ነበር የተባለችው ከተማ በሴራሚክ ምርት ማዕድን መገኛነት ትታወቃለች ።
የሩሲያ ጦር 18 ወራት የፈጀበት በከተማዋ 36 ድልድዮች ይኖሩ ስለነበር ዩኬራኖች እነኝህን እንደከለላ ይጠቀማቸው እንደነበረ እና እንደ ባክሙት ውድመት እንዳይደርስ በመታሰቡ ነው ተብሏል።
የሩሲያ ጦር አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሬያለሁ ቢልም በምዕራብ የከተማው ዳርቻ የዩክሬን ሀይሎች አሉ ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል ። የራሽያ ሚዲያዎች ግን ሙሉ ለሙሉ ጦሩ ተቆጣጥሮታል በማለት ላይ ይገኛል ። ይህም 70% የዶንዩስክ ግዛትን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ አስችሏታል ።
