“ሰላም በብዝኅ ሃይማኖት ማኅበረሰብ” የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

Date:

በሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የተሰናዳ “ሰላም በብዝኅ ሃይማኖት ማኅበረሰብ” የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዚያ 4 2017 ዓ.ም ተመርቋል።


በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ; ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብባዊ ዞን ማይጨው ሀገረ ስብከት ; እና በመንበረ ፓትርያርክ የቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር እና የማኅበራት ማደራጃ፣ ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኸይረዲን ተዘራ ; የቤተእምነት መሪዎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
ዶ/ር ኸይረዲን ተዘራ እንደገለጹት የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ እንደመሆኑ የእያንዳንዱ ሰው አስተዋፆ ለሰላም ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው መጽሐፉ ጸሐፊው ለሰላም በሚደረገው ሂደት ላላቸው አስተዋፆ ገጸ በረከት እንደሆነ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው መጽሐፉ ለሀገራዊ ምክክሩ ግብዓት ሆኖ እንደሚያገለግል ጠቁመዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የኪነጥበብ ሰዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...