ሱዳን በጦርነቱ ዳፋ አንዳንድ ቤተሰቦች ሣር እየበሉ ነው

Date:

የሱዳን ጦር ሠራዊት (SAF) ካርቱም ከተማ የሚገኘውን ቤተመንግሥት በመቆጣጠር በሁለት ዓመቱ የርስ በርስ ጦርነት ወሳኝ የተባለውን ድል መቀዳጀቱ ተነገረ ። የሱዳን መንግሥታዊ ቴሌቪዥን ጦሩ ቤተመንግሥቱን ያስለቀቀው ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) መሆኑን ዛሬ ማለዳ ዘግቧል ። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቤተመንግሥቱን ጨምሮ የሱዳን በርካታ ሰፈሮችን ለበርካታ ጊዜያት ተቆጣጥሮ ነበር ።

በሁለቱ የሱዳን ኃይላት መካከል ጦርነቱ ከዛሬ ሁለት ዓመት ግድም ማለትም (ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2015 ዓ.ም) ከተቀሰቀሰ በኋላ ቤተመንግሥቱ ወዲያውኑ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ቁጥጥር ወድቆ ነበር ። ይህ ድል ለሱዳን ጦር ሠራዊት ታላቅ እመርታ እንደሆነ ቢገለጥም፤ ፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ የካርቱም ደቡባዊ ክፍልን እና በዋና ከተማዪቱና ተጎራባቿ ኦምዱርማን ከተማ መካከል ያሉ ቦታዎችን አሁንም እንደተቆጣጠረ መሆኑ ተዘግቧል ።

ሁለት ዓመት በተጠጋው የሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ከ28,000 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘግቧል ።  ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ። ጦርነቱ በፈጠረው ረሐብ የተነሳ አንዳንድ ቤተሰቦች በሕይወት ለመቆየት ሣር እየበሉ መሆናቸውን የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል ። 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...