ፑቲን እና ትራምፕ በስልክ ተወያዩ

Date:

ውይይቱ ወዳጃዊ እና ግልጽ እንደነበር እንዲሁም ለ55 ደቂቃዎች መቆየቱን የክሬምሊን ረዳት ኡሻኮቭ አስታውቀዋል።

ፑቲን ለትራምፕ 80ኛ ዓመት የልደት በዓል የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ ሀገራት ተወካዮች መካከል ሊደረጉ ስለሚችሉ ግንኙነቶችም ተወያይተዋል።

በውይይቱ ​የተደረጉ ቁልፍ ንግግሮች፦

​▪️ ትራምፕ በፑቲን የስልክ ጥሪ እጅግ መነካታቸውን በመግለጽ፤ ፑቲን ወደ ዋይት ኋውስ በመደወል የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

​▪️ ዊትኮፍ እና ኩሽነር በቅርቡ በሩሲያ ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡

​▪️ ሁለቱ መሪዎች በዋና ዋና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እና በአሜሪካ-ሩሲያ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡

​▪️ ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ግጭት የማስቆም አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

​▪️ ትራምፕ ለቀውሱ እልባት ለመስጠት በአውሮፓ ሀገራት እና በኪየቭ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

​▪️ በውይይቱ ወቅት የአሜሪካ እና የኢራን የመግባቢያ ስምምነት ጉዳይም ተነስቷል፡፡

​▪️ ትራምፕ የአሜሪካ እና የኢራን ስምምነት መቃረቡንና በቅርቡ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

​▪️ ፑቲን በኢራን ዙሪያ ያለው ውጥረት እየረገበ በመምጣቱ የተሰማቸውን እርካታ አጋርተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...