ምንም እንኳን ሁለቱ አገራት በአሜሪካ አማካኝነት ተኩስ አቁም ቢያደርጉም በሱዌዳ ያለው ግጭት አሁንም ቀጥሏል ተብሏል።
በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር በዋሽንግተን ጥረት የተደረሰው ተኩስ አቁም በዮርዳኖስ እና ቱርክ ጎረቤቶች ድጋፍ አግኝቷልም ብለዋል።
በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር ቶም ባራክ በኤክስ ገፃቸው ላይ ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
ባራካ “አሜሪካ ድሩዞች፣ ቤዱዊንሶች እና ሱኒዎች የጦር መሳሪያቸውን እንዲፈቱ ጥሪ ታቀርባለች” ማለታቸውም ተሰምቷል።
ሁሉም ሀይሎች አዲሷን እና አንድነቷ የተጠበቀ ሶሪያን በመፍጠር መረባረብ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል አምባሳደሩ።
ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ በጉዳዩ ላይ የእስራኤልና የሶሪያ ፖለቲከኞች ያሉት ነገር የለም።
በደቡብ ምዕራብ ሶሪያ በሡዌይዳ ግዛት ያለ፣ በድሩዞችና ቤዱዌን መካከል ያለው ውጥረት አሁንም እንዳልረገበ ተወስቷል።
ሶሪያ እና እስራኢኤል ተኩስ አቁም ላይ ደረሱ
Date:
