በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን “American Space” ማዕከል በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
በአሜሪካ ኤምባሲ ድጋፍ የተገነባው ማዕከሉ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ተመራማሪዎች እንዲሁም ለአካባቢው ወጣቶች በምርምር፣ በቴክኖሎጂና በዲጂታል ክህሎት ዘርፍ የተለያዩ ነጻ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
ማዕከሉ ፦
– የነጻ ኢንተርኔትና ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት፣
– በአሜሪካ የትምህርት ዕድሎች ላይ መረጃና ምክር፣
– በSTEM፣
– በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣
– በሮቦቲክስ፣
– በዲጂታል ክህሎት እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠናዎችን ያቀርባል።
በተጨማሪም በአመራር፣ በሙያ ክህሎት፣ በፈጠራ ሥራ እና በሚዲያ እውቀት ላይ ያተኮሩ ውይይቶችና ወርክሾፖች ይካሄዳሉ።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ እና ሌሎች የክልሉና የከተማው ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ ማዕከሉ ወጣቶችን በቴክኖሎጂና በምርምር ዘርፍ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የሲዳማ ክልልና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችም ማዕከሉ ለተማሪዎች፣ ለተመራማሪዎችና ለወጣቶች የዓለም አቀፍ የእውቀትና የክህሎት ዕድሎችን እንደሚያሰፋ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
