በህንድ ካሽሚር በቱሪስቶች ላይ በተከፈተ ጥቃት ቢያንስ 26 ሰዎች ተገደሉ

Date:

በህንድ ጃሙ እና ካሽሚር ግዛት ውስጥ ታጣቂዎች  በቱሪስቶች ላይ በከፈቱት ጥቃት 26 ሰዎች ሲገደሉ ሎሎች 17 ሰዎች መቁሰላቸውን እሮብ እለት ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ በመግለጫው ኡክሎ እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ከተፈፀመ አስከፊ ጥቃት መካከል አንዱ ሲሆን በህንድ እንዲህ ዓይነት ክስተት ሲያጋጥም ከሁለት አስርት ዓመታት በኃላ ነው ተብሏል። ጥቃቱ በፓሃልጋም በተሰኘው አካባቢ በሚገኝ ሜዳማ ስፍራ ሲሆን ከሞቱት ሰዎች መካከል 25 ህንዳውያን እና አንድ የኔፓል ዜጋ መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል።

እ.ኤ.አ. ከ2008 የሙምባይ ግድያ በኋላ በህንድ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የከፋው ጥቃት ተብሏል። ጥቃቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሳዑዲ አረቢያ የሁለት ቀናት ጉብኝታቸውን አቋርጠው ረቡዕ ጠዋት ወደ ኒው ዴሊ ተመልሰዋል። የገንዘብ ሚኒስትሯ ኒርማላ ሲታራማን የዩናይትድ ስቴትስ እና የፔሩ ጉብኝታቸውን “በዚህ አስቸጋሪ እና አሳዛኝ ጊዜ ከሕዝባችን ጋር ለመሆን” በሚል ማሳጠራቸውን ተናግረዋል።ሞዲ በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከብሄራዊ ደህንነት አማካሪያቸው፣  ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የመከሩ ሲሆን ልዩ የደህንነት ካቢኔ ስብሰባ መጠራታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ጥቃቱ ሞዲ እና የሂንዱ ብሄረተኛ የባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ የጃምሙ እና ካሽሚርን ከፊል የራስ ገዝ አስተዳደር በመሻር እና ለረጅም ጊዜ ችግር ውስጥ ለነበረው ክልል ሰላም እና ልማት ለማምጣት ትልቅ ስኬት ነው ብለው ለገመቱት በሙሉ እንደ ውድቀት ተቆጥሯል።ብዙም እውቅና የሌለው ታጣቂ ቡድን የሆነው “የካሽሚር ተቃዋሚ” ለጥቃቱ ሃላፊነቱን መውሰዱን በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፈው መልእክት ገልጿል። በክልሉ ከ85,000 በላይ ሰዎች እንዲሰፍሩ መደረጉ ቅሬታውን ገልጿል፣ ይህም “የሕዝብ ለውጥ” እንዲፈጠር አድርጓል ብሏል። ቡድኑ በሰጠው መግለጫ “የተጠቁት ግለሰቦች ተራ ቱሪስቶች አልነበሩም፣ ይልቁንም ከህንድ የፀጥታ ኤጀንሲዎች ጋር የተገናኙ እና የተቆራኙ ናቸው” ብሏል።

@ዳጉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...