በትግራይ ክልል የአንድን ገበሬ ፍየል በመስረቅ አርዶ ሲበላ እጅ ከፈንጅ የተያዘው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

Date:

በትግራይ ክልል ሰሜን ምእራብ ዞን ፅምብላ በተሰኘ ወረዳ ልዩ ስሙ ደብረ አባይ በተባለ አካባቢ ተከሳሽ ወጣት ሓጎስ ሙላው ገብረማርያም በመባል የሚታወቅ ሲሆን ንብረትነቷ የአንድ ገበሬ የሆነችን ፍየል ምቹ ጊዜና ቦታ መርጦ አርዶ ለመብላት በመሞከርበት ወቅት የፀጥታ አካላትና የአከባቢው ማህበረሰብ በመቀናጀት በሰሩት ስራ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ ፍየሏን አርዶ ለመብላት ያስፈልጉኛል ያላቸውኝ መሳርያዎችና ለማጣፈጫነት ያገለግላሉ ያላቸውን የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን አዘጋጆቶ ፍየሏን አርዶ ለመብላት በዝግጅት ላይ እያለ ነው የተያዘው።ታድያ ጉዳዩ ሲከታተል የቆየው የወረዳው ፍርድ ቤትም ግለሰቡ በ1 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መስጠቱን ከዞኑ የፖሊስ መምርያ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በተያያዘ ጉዳይ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ/ም በ ዓዲ ዳዕሮ ወረዳ ከአንድ ገበሬ ሶስት ከብቶችን ሰርቀው ከአከባቢው ለመሰወር የሞከሩ ገብረ ካህሳይ ያይንሸትና ተስፋይ ንርአ ተወለ በመባል የሚታወቁ ሁለት ግለሰቦች የአከባቢው ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተከትሎም የወረዳው ፍርድ ቤት ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ/ም ባዋለው ችሎት ተከሳሾቹ በፈፀሙት ተግባር ጥፋተኛ ናቸው በማለት አንደኛ ተከሳሽ ገብረ ካህሳይ ያይንሸት በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ተስፋይ ንርአ ደግሞ በሰባት ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ መሰጠቱን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

በሚሊዮን ሙ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...