“በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የተሰማሩ” 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

Date:

“በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ ተሰማርተዋል” የተባሉ የ123 ተጠሪጣሪዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ መደረጉን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።

“የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በርካታ ሰው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን በህጋዊ መንገድ እያካሄደ መሆኑ በእጅጉ የሚበረታታ ነው” ያለው አገልግሎቱ “ነገር ግን አንዳንድ አካላት አሁንም ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ለማትረፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን በክትትል ደርሼበታለሁ” ብሏል።

በዚህም መሠረት በተለያየ ደረጀ “በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሰማሩ” የ123 ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ ትናንት መስከረም 9/2018 ታግዶ የህግ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም አንዳንድ የባንክ ባለሙያዎች በጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ የክትትል መረጃው ውጤት የሚያመላክት በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ መግለጹን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ቀደም ሲል በተመሳሳይ “ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች” የባንክ ሒሳብ መታገዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት በወቅቱ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት በሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓት በኩል እንዲከናወን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑን ገልጾ በህገ ወጥ መጠቀም የንብረት መወረስን ጨምሮ በከፍተኛ ጽኑ እስራት እንደሚያሰቀጣ አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢ-መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ መግለጻቸው አይዘነጋም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...