በሕገ መንግሥቱ መሠረት እና በሕዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሠረተ መሆን

Date:

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም ስሱ እና ውስብስብ ከሆኑት ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ የክልል ድንበር፣ የሕዝብ ቆጠራ፣ የመቀመጫ ድልድል እና የበጀት ክፍፍል ናቸው።

የዛሬው የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለብዙዎች አዲስ ነገር ለምን እንደሆነ አልተረዳሁም። የ2013 ዓ.ም (ወይም 2021 እ.ኤ.አ) ምርጫ ለማድረግ ለ23 ቀናት ጎንደር ስልጠና ለመስጠት እኔ ከPMo ፤አደም ፋራህ በውቅቱ (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ነበ ከየፌዴሬሽን ምክር ቤት) ፣ ና አንዲት ሴት ተመድበን ነበር፡፡

እናንም ሞላ በወቅቱ የጎንደር ከተማ ከንቲባ እና በወቅቱ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አገኘሁ ተሻገር እንዲሁም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎሀ ሆቴል ምሳ እየበላን በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ስናደርግ እንደነበረን አስታውሳለሁ። ወልቃይት፣ ራያ፣ ና ሌሎችም አካባቢዎች ውዝግብ ውስጥ የገቡ ናቸው።

ውዝግቡ ደግሞ የድንበር መሬት ብቻ አይደለም፤የማንነትም ብቻ አይደለም፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን መቀመጫዎች፣ የፌዴራል በጀት ድልድልን እና ሌሎች ሀብቶችን ስለሚነካም እንጂ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የሚመደበው በየክልሉ ባለው ሕዝብ ብዛት ላይ በመመስረት ስለሆነ። አንድ ክልል የሚቆጥረው ሕዝብ ቁጥር ከፍ ባለ ቁጥር የሚልከው ተወካይ ቁጥር ይበዛል። ከዚህ ባሻገር ደግሞ የፌዴራል በጀት ሲከፋፈል ከግምት ውስጥ ከሚገቡት ምክንያቶች አንዱ የሕዝብ ብዛት ስለሆነ።

ይህ ማለት እንደ ወልቃይት ያሉ አካባቢዎችን በሕጋዊ መንገድ የሚያስተዳድረው ክልል፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ተጨማሪ መቀመጫዎችን ያገኛል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የፌዴራል በጀት ሲከፋፈልም ተጨማሪ ድርሻ ያገኛል።

ስለዚህ የድንበር ውዝግብ ማለት በዋናነት የሥልጣን፣ የውክልና እና የሀብት ክፍፍል ውዝግብ ማለትም ነው። ይህንን ሁኔታ ከኬክ ጋር ብናመሳስለው ማንኛውም ክልል ከሚቀረበው ኬክ ላይ ትልቁን ቁራጭ ለማግኘት ይፈልጋል ማለት ነው፡፡

የሆነ ሆኖ እነዚህ አካባቢዎች አወዛጋቢ በመሆናቸው በፌዴራል መንግሥት እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) ቁጥጥር ሥር ሊተዳደሩ እንደሚገባ የሚነሱ ሀሳቦችም ከክርክርና ከጥያቄ ውጨ መሆነ አይችሉም፡፡


የፌዴራል መንግሥት አንድን ክልል ለማስተዳደር ሲረከብ፣ የዚያ ክልል ሕዝብ በሕገ መንግሥቱ መሠረት በራስ የመተዳደር መብቱ እንደተጣሰ ሊሰማው ይችላል።ወይም እንደዛ ሊቆጠር ይችላል፡፡

በተጨማሪም፣ ይህ ሁኔታ በፌዴራልና በክልል መካከል ያለውን የሥልጣን ክፍፍል በተመለከተ አዲስ ክርክር ይፈጥራል። አንዳንዶች ይህን ከአንድ ትልቅ የቤተሰብ ግጭት ጋር ያመሳስሉታል፤ ወንድሞች በንብረት ሲጨቃጨቁ ሽማግሌው ጣልቃ ገብቶ ንብረቱን ለጊዜው እንደሚይዝ አይነት ተመሳሳይነት አለው ይላሉ።

ነገር ግ ን ሽማግሌው ሁሉን አዋቂ እና ገለልተኛ ቢሆንም፣ ውሳኔው በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትግ ን አለበትየሚለው መሰመር ያለበት ይመስለኛል፡፡ ጌች ፖለቲካው ጠፋበት መሰለኝ

ለዘለቄታው መፍትሄው በሕገ መንግሥቱ መሠረት እና በሕዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሠረተ መሆን ያለበት ይመስለኛል፡፡ በተረፈ የዛሬው ውሳኔ በ2013 የማውቀ ነው ለማለት ነው።

ከዮናስ ዘዉዴ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...