በሕጻጽ መጠሊያ ጣቢያ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

Date:

ሁለቱ ፓርቲዎች ኢሕአፓና ስምረት ሲሆን ያወጡትን መግለጫም ለአዲስ ማለዳ ልከውላታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ባወጣው መግለጫ አሰቃቂውን ጦርነት ተከትሎ ከቤታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያው ያሉ ንጹሀን ዜጎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ሲደርስባቸው መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ችግሮቻቸውን የሚፈታላቸው ብቻ ሳይሆን ጉዳዬ የሚላቸውም አካል ባለመኖሩ ለከፋ አደጋ ከተጋለጡ ዓመታት አልፈዋል የሚለው መግለጫው በሕፃፅ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ላይ የደረሰውም ይሄው ነው ብሏል።

ነገር ግን ረሃብ በፍጹም ጊዜ አይሰጥምና ለእነዚህ ወገኖች በአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርሳቸውና ጉዳያቸውም በዘላቂነት እንዲፈታ ኢሕአፓ ጠይቋል፡፡

የኢሕአፓ መግለጫ ሲቀጥል ልጆቻቸው በጦርነት ለተማገዱባቸው፤ ጥቂቶች ለስልጣናቸው ሲሉ ከቀያቸው ላፈናቀሏቸው ለእነዚህ ዜጎች የሚደረግ ማንኛውም ድጋፍ እርዳታ ሳይሆን የዜግነት ግዴታ እንደሆነም ሊሰመርበት ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

የጌታቸው ረዳ ስምረት ፓርቲም በተመሳሳይ ያወጣውን መግለጫ ለአዲስ ማለዳ ልኮላታል፡፡

ስምረት በምዕራብ ትግራይ ዞን አስገደ ወረዳ ሕጻጽ የተፈናቃዮች መጠለያ ነዋሪዎች ረሃቡን ለማስቆም እና ወዲያውኑ ለመድረስ ሰብአዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብሏል።

ኋላ ቀር ቡድን እያለ የጠራው ህወሓትን ከሕዝቡ በፊት የማዳን መዝሙር በሰብዓዊነት፣ በህሊና፣ በሥነ ምግባር እና በሕግ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ሕዝባችን በዚህ ጽንሰ ሐሳብ እየሞተ ነው ሲልም አክሏል።

ስምረት ሁሉም የሰብአዊ ድርጅቶች ይህንን አሳዛኝ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱት ጥሪ አቅርቧል፡፡

ይህ ሁኔታ ከሚዲያ ካልተደበቀ በስተቀር በሌሎች አካባቢዎች የተፈናቀሉና የተሰደዱ ወገኖቻችንም የመሰቃየትና የመሞት ኣደጋ እንደተጋረጠባቸዎ ምንም ጥርጥር የለውም ሲልም አትቷል፡፡

“ ህዝባችንን በተሳሳተ መንገድ በመንቀሳቀስ ወደዚህ ደረጃ ያደረሱት ኋላቀር ቡድን እና ተባባሪዎቹ አሁንም የፕሪቶሪያን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ወደ ቤታቸው ለመመለስ ዘላቂ መፍትሄ የሆነውን ህገ መንግስት ለማክበር እየተቸገሩ ነው፤ የትግራይን ህዝብ “በእስር” ውስጥ አስገብቶ ሁሉንም ነገር በስልጣን እና በቡድን ጥቅም ላይ በማዋል የፖለቲካ ቁማር ተጫውቷል፤ እየተጫወተም ይገኛል ” ሲል ወንጅሏል፡፡

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ክልሎች፣ የኢትዮጵያ መንግስት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለተፈናቀሉ እና በአጠቃላይ ለስደተኞች እና በተለይም በህፃፅ ላይ ለደረሰው ከባድ ረሃብ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል፡፡

አዲስ ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...