በመዲናዋ 689 አሽከርካሪዎች እየተፈለጉ ይገኛሉ

Date:

እነዚህ ተሽከርካሪዎች የሰው ህይወት ያጠፉ ፤የ ንብረት ጉዳት ያደረሱ ናቸው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በቅርቡ ባበለፀገው አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት ሲስተም በኩል የሁሉንም አሽከርካሪዎች መረጃዎችን እንደሚከታተልም አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚዴቅሳ ፤ ተቋሙ ሪፎርም ውስጥ እንደነበር ዛሬ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።

ከሪፎርሞቹ አንዱ የቴክኖሎጂ ስራዎች መሆኑን የሚናገሩት ዋና ዳይክተሩ፤ የትራፊክ ቁጥጥሩን ዘመናዊ ማድረግ እና ማሻሻል ደግሞ ዋነኛው ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ከጥር አንድ ጀምሮ ወደ ትግበራ የገባው አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት እና ማኔጅመንት ሲስተም የደንብ ጥሰት እንዲቀንስ፣ለወረቀት ይወጣ የነበረውን 17 ሚሊየን ብር ማስቀረት መቻሉም ተገልጿል።

በከተማዋ ያሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም መንጃ ፍቃዳቸውም ከዚህ የሆኑ አሽከርካሪዎችም በዚህ ሲስተም ውስጥ መግባታቸው የተነሳ ሲሆን ሁሉንም በዚህ ሲስተም መቆጣጠር መቻሉም ተነስቷል።

በዚህ ሲስተም ከክልል ወደ አዲስ አበባ የሚገባ ተሽከርካሪም ደንብ ሲተላለፍ ሲስተሙ እንደሚመዘግብም ተነስቷል።

ሲስተሙ ወደ ትግበራ ከገባበት ቀን ጀምሮም 2ሺ4 መቶ61 ደንብ ተላላፊዎች በዚህ ሲስተም ተቀጥተዋል።
ከደንብ ተላላፊዎቹ 1ሺ4 መቶ58 ቅጣት የተላለፈባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው መክፈልም ችለዋል።

7መቶ 72 ሺ 7 መቶ 40 የሚሆኑ አሽከርካሪዎች በዚህ አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት ሲስተም ውስጥ መግባታቸውም ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ ባለፉት 9 ወራት ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ከቅጣት ማገኘቱንም ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...