ትላንት እና ዛሬ በተደረገ 4 ዙር በረራ የተመለሱት 5መቶ69 ወንዶች፣ 3መቶ77 ሴቶች ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 45ቱ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸዉ፡፡
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡
ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመላክተዉ፤ መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 1 ሺህ 46 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
