ኢትዮ ቴሌኮም እና የመድኃኒት አቅራቢዉ በዲጂታል መፍትሄዎች ለማዘመን ተስማሙ

Date:

​ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር ዘመናዊ የዲጂታል ጤና አቅርቦት ሰንሰለት ሶሉሽን ለመተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ ትብብር የመድኃኒት እና የህክምና ቁሳቁሶች ስርጭትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማቀላጠፍ አሰራሩን የበለጠ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ስምምነቱ የአቅርቦት ሰንሰለቱን በ AI-የታገዘ የደህንነት ስርዓት፣ በስማርት ቪዲዮ ትንተና፣ በዘመናዊ የቁጥጥር ክፍሎች እና በኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያ በማሻሻል ፈጣን እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለማድረግ ያግዛል።

ዛሬ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም የተፈረመው ይህ ስምምነት የስራ ጫናን መቀነስ፣ የመድኃኒት ቁጥጥርን ማሻሻል፣ እና የእቃ ክምችት ስርዓት ትክክለኛነትን ማሳደግን ጨምሮ በርካታ አዎንታዊ ውጤቶችን ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...