የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ፣ ጋዜጠኞቹን በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ ለ2ኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ቀጠሮ እንዲሰጠው ቢያመለክትም ጉዳዩን ያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በ50,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁ መስከረም 7/2018 ዓ.ም ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በውሳኔው ቅር የተሰኘው ፖሊስ በይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት አመልክቷል፡፡
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ የወንጀል ይግባኝ ችሎት ፣ ዛሬ በዋለው ችሎቱ ፣ የፌዴራል ፖሊስና የጋዜጠኞቹን ጠበቃ አቤቱታ ካዳመጠ በኋላ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 14 ቀን 2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የሸገር ሬዲዮ ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ፀጋው በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ዛሬ 20ኛ ቀናቸው ነው፡፡
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
