በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ከ50 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር መቀጣታቸውን የመዲናዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ከበበው ሚዴቅሳ እንደገለጹት፤ ሕግ የሚጥሱ አሽከርካሪዎች ላይ የቁጥጥር ሥራዎች ተሠረርተዋል።
በዚህም ከ50 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ አሽከርክረው ተቀጥተዋል ብለዋል።
በተጨማሪም 7 ሺህ 643 ደህንነት ቀበቶ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች፣ 746 ሞተር አሽከርካሪዎች ያለሄልመት በማሽከርከር፣ 41 ሺህ 373 የብዙሀን ትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ላይ ተሽከርካሪ በማቆም እንዲሁም የሚከለክሉ ቦታዎች ላይ የቆሙ 33 ሺህ 638 አሽከርካዎች የተቀጡ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በአጠቃላይ በተሰራ የትራፊክ የሕግ ማስከበር እና የቁጥጥር ስራ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንብ በመተላለፍ ተቀጥተዋል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ጋር በመሆን 19 ሺህ 192 ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ የመንገድ ላይ የቴክኒክ ምርምራ የተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከነዚህም ውስጥ የቴክኒክ ጉድለት ያለባቸው 3 ሺህ 220 አሽከርካሪዎች እንዲቀጡ ተደርል ብለዋል።
