በትግራይ በሦስት ወራት ውስጥ 310 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ከወጪ ንግድ ተገኝቷል

Date:

በትግራይ ክልል ከተቀመጠው መመሪያ ውጭ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ተያያዥ ጥፋቶችን ሲፈፅሙ በተገኙ ከ74 ሺሕ 800 በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

የትግራይ ክልል ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ በላከው መረጃ፤ በተያዘው የ2018 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ውስጥ ብቻ ከመመሪያ ውጭ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች፣ ምርት በሚደብቁ እና መሰል ጥፋት ሲፈጽሙ በተገኙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ  መውሰዱን ገልጿል።

ተቋሙ ሕገ-ወጦችን በመከላከልና በመቆጣጠር፣ ንግድን በማነቃቃትና በማጠናከር፣ የአቅርቦት ተደራሽነትና ፍትሓዊነትን ለማረጋገጥ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት መመሪያን መሠረት ያደረገ እና ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ የምርት አቅርቦት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።

እርምጃ የተወሰደውም በንግዱ ዘርፍ ላይ የምርት እጥረት እንዳይገጥም እና ሕገ-ወጥ ሥራን ለመከላል በተደረገው ክትትል መሰረት መሆኑን መረጃው ያሳያል።

በሦስት ወራት ውስጥ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ከታቀደው 123 ሺሕ 550 በላይ ነጋዴዎች ወደ 98 ሺሕ በሚሆኑት ላይ ክትትል ማድረግ መቻሉን ቢሮው አመላክቷል።

በዚህም ክትትልና ቁጥጥር ከተደረገባቸው 74 ሺሕ 819 ነጋዴዎች ውስጥ፤ የተለያዩ የአሰራር ጥሰቶች እንዲሁም ጥፋቶች መፈፀማቸውን አረጋግጫለሁ ሲል ገልጧል።

በዚህም መሠረት እርምጃ የተወሰደባቸው ነጋዴዎች የቃልና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ድርጅታቸው እንዲታሸግ ማድረግ፣ ንግድ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ እና በሕግ እንዲቀጡ መደረጉን የክልሉ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ በላከው መረጃ አስታውቋል።

በተያያዘ መረጃ በሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ከሰሊጥ፣ ከጨርቃ ጨርቅና ማዕድን ዘርፍ የወጪ ንግድ 309 ሚሊዮን 654 ሺሕ 410 ዶላር ገቢ መገኘቱን የትግራይ ክልል ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ኤጀንሲው የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የሚችሉ ምርቶች እና ማዕድናትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ገቢ ለመሰብሰብ በዘርፉ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ ክትትል የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በዚሁም መሰረት የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የሚችሉ የቅባት እህሎች በጥራት ተመርተው በሕጋዊ የግብይት ሰንሰለት እንዲሸጡ በማድረግ፣  የሚያመርቱ ኢንዳስትሪዎችን በመደገፍና የማእድን ዘርፉን በማበረታታት ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

በተለይም የወርቅ ግብይትን በሕጋዊ መንገድ ወደ ብሄራዊ ባንክ እንዲገባ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ መረጃው አመላክቷል፡፡

በወጪ ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ እንደሚገኝ እና እስከአሁን በዚህ ሦስት ወር ውስጥ በመቐለ ጉምሩክ በኩል ወደ ውጪ የተላኩት የሰሊጥ ምርቶች 282 ሺሕ 150 ዶላር፣ ከጨርቃ ጨርቅ ደግሞ 1ሚሊዮን 919 ሺሕ 902 ዶላር  እንዲሁም ከወርቅ 307 ሚሊዮን 3 27 ሺሕ 157 ዶላር  የተገኘ ሲሆን፤ በድምሩ 309 ሚሊዮን 654 ሺሕ 410 ዶላር ከወጪ ንግድ መገኘቱን የክልሉ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ አመላክቷል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...