በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ሰላማዊ ሰልፍ ሊካሄድ ነው

Date:

በትግራይ ክልል የሕወሃት አመራሮችና የፌዴራል መንግሥት በደረሱበት አለመግባባት የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ፣ ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ መታቀዱን “በትግራይ ለውጥ ፈላጊ” የተባለው ስብስብ አስታውቋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎችንና ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ያቀፈው ይህ ስብስብ፣ ባለፈው ቅዳሜ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታና መፍትሔዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።

የለውጥ ፈላጊ ስብስቡ አባል ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ፤ “በትግራይ ክልል በዳግም ጦርነት ደም መፋሰስ እንዳይፈጠርና ልዩነቶች በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

አሁን ያለው የሕወሃት ቡድን የትግራይን ሕዝብ እንደማይወክልና በክልሉ እንደሚጀመር እየተሰጋ ያለው ጦርነት የውጭ ኃይሎች ድጋፍ እንዳለበት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ለኤምባሲዎች ለማሳወቅ በቀጣዮቹ ሳምንታት ሰላማዊ ሰልፉ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

የባይቶና ዓባይ ትግራይ ፓርቲ አባል ዶክተር ፀጋዘአብ ካሱ በበኩላቸው፤ የክልሉ ነዋሪዎች እና ወጣቱ ጦርነት እንደማይፈልግ ተናግረዋል።

ባይቶና በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ አመራሮች መካከል ያለውን ችግር ለማቀራረብ ጥረት እያደረገ መሆኑንና መንግሥት በክልሉ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዳያቋርጥ የማድረግ ሥራዎች ውጤታማ እንደሆኑለት ተናግረዋል።

ጥቂት የሥልጣን ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች የሚፈጥሩት ውጥረት የሕዝቡ ፍላጎት አለመሆኑን ለማሳወቅ እየተሰራ እንደሆነ የተናገሩት ዶክተር ፀጋዘአብ፤ “ከፌዴራል መንግሥት ጋር መሥራት ግዴታ ነው” ብለዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...