በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ የ30 በመቶ ግብር በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል

Date:

​ የገንዘብ ሚኒስቴር ከ2018 የበጀት ዓመት ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ 30 በመቶ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማረጋገጡ ተሰማ። ይህ አዲስ ግብር 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15 በመቶ የኤክሳይዝ ቀረጥን የሚያካትት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህ እርምጃ በአገሪቱ የፋይናንስ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑና የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

​ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባቀረቡት አጠቃላይ የዜጎች በጀት ዉስጥ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የግብር አይነቶችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።

​በዚህ መሰረት፣ ከነዳጅ ላይ ከሚጣለው አጠቃላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ በተጨማሪ፣ የንብረት ታክስ ይገኙበታል። እንዲሁም አማራጭ አነስተኛ ታክስ እና የቅድመ ግብር ክፍያ በተመሳሳይ መልኩ በ2018 በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።

​ነዳጅ በማዕከላዊነት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የግብር ጭማሪው የዋጋ ግሽበቱ እንዲባባስ ያደርጋል የሚል ስጋት ሲከሰት እንደነበር ይታወሳል።

CapitalNews

ዝርዝሩን ያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...