በመጋቢት ወር በተደረገ ጥናት የፆታ እኩልነት ስጋት 60 በመቶ መጨመሩንና ከአራት ሀገራት አንዱ የሴቶችን መብት የመፃረር አዝማሚያ እንደሚያሳይ ተገልጿል፡፡
ከ 6 መቶ ሚሊየን በላይ ሴቶችና ልጃገረዶች አሁንም በግጭት ቀጠናዎች አካባቢ እንደሚኖሩ እና ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት መጨመሩንም ጠቁሟል።
እንደዚህ ያሉ ክስተቶች ባለፉት አመታት የተገኙ ስኬቶችን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብሏል ሪፖርቱ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴቶች አስራ አምስተኛ አመቱን ሲያከብር በዓለም ዙሪያ ያሉ ከአራት ቢሊየን በላይ ሴቶች እና ልጃገረዶች የፆታ እኩልነት ዉስጥ እንዲካተቱ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታዉቋል፡፡
የሴቶችን መብት የሚፃረር እንቅስቃሴን መዋጋት ፣የሰላም ግንባታ ጥረቶችን መጨመር ፣ ሴቶች በሰላም ንግግሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ፣ የኢኮኖሚ አለመመጣጠንን መፍታት የዕቅዱ አካል ሲሆን፤ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መቃወም እና የሴቶችን የትምህርት ፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋት ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴቶች/ዩኤን ዉሜን/ ለፆታ እኩልነት ተጨማሪ ኢንቨስትመንት አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ፤ የመንግስት እና የግል ሴክተሮች ለሴቶች መብት ድጋፍ የሚሰጡትን የገንዘብ ድጋፍ እንዲጨምሩ አሳስቧል።
