በአዲስ አበባ ለጨረታ ለቀረቡ ቦታዎች በካሬ ሜትር 265 ሺሕ ብር መሰጠቱ ታወቀ

Date:


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬትና ልማት አስተዳደር ቢሮ ለጨረታ ካቀረባቸው 427 ቦታዎች ውስጥ፣ የቀረበው ከፍተኛ ዋጋ በካሬ ሜትር 265 ሺሕ ብር መሆኑና ቦታውም ካዛንቺ እንደሆነ ታወቀ፡፡፡
የመሬትና ልማት አስተዳደር ቢሮ የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በአምስተኛ ዙር እየተካሄደ በሚገኘው የመሬት ሊዝ ጨረታ 18 ሔክታር መሬት ቀርቧል፡፡
በሊዝ ለማጫረት ከቀረቡ ቦታዎች ውስጥ ካዛንቺስ የሚገኝ አንድ ቦታን በካሬ ሜትር 265 ሺሕ ብር ለመግዛት ከተጫራች ዋጋ መቅረቡን፣ እስካሁን በአምስት ክፍላተ ከተሞች በተደረገው የጨረታ ሒደት 76 ተጫራቾች በጊዜያዊነት ጨረታውን ማሸነፍ መቻላቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡
ለጨረታው የቀረቡ ቦታዎች የሚገኙት በዘጠኝ ክፍላተ ከተሞች እንደሆኑ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በአጠቃላይ የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የተጫረቱት ብዛት 6,885 ተጫራቾች  እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
@ሪፖርተር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...