በመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊስ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ብቃት ምዘና ሀምሌ 1/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ ፍቅርተ አበራ ተናግረዋል፡፡
በተመረጡ ተቋማት ተጀምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ 170ሺ ሰራተኞች የብቃት ምዘና ያደርጋሉል/ይወስዳሉ፡፡ ባለፈው አመት የመዋቅራዊ ማሻሻያ ሲደረግ ሰራተኞች ያላቸውን እውቀት እና ክህሎት በፈተና የማረጋገጥ ስራ ሲሰራ ቆይቷልም ተብሏል፡፡
የብቃት ምዘናው አላማ ሰራተኞች ያሉበትን ደረጃ (የባህሪም ሆነ የቴክኒካል እውቀታቸውን) መለየት ሲሆን በብቃት ምዘናው መሰረት ተወዳዳሪ እና ምንም ችግር የሌለባቸው ሰራተኞች ወደ ማትጊያ ስርዓት ይገባሉ፡፡ ክፍተት ያለባቸው ደግሞ እንደ ክፍተታቸው ተለይቶ ስልጠና በመስጠት እንዲመዘኑ ይደረጋል ብለዋል ም/ቢሮ ኃላፊዋ ፍቅርተ አበራ፡፡
