በአዲስ አበባ ከ75 እስከ 80 በመቶ ታክስ አሰባሰብ ግምት ላይ የተመሰረተ እደሆነ ተገለጸ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ  በከተማዋ ከ75 እስከ 80 በመቶ የታክስ አሰባሰብ ግምት ላይ የተመሰረተ እደሆነ ገልጿል፡፡

በቢሮው የታክስ ኦዲት ዳይረክተር አቶ ጌታቸዉ ግርማ፤ግብር ከፋዩ አሁን ላይ ግብሩን እየከፈለ ያለዉ የተደራጀ ሰነድ ይዞ ሳይሆን በግምት ነዉ ብለዋል፡፡

አቶ ጌታቸዉ  ብዙ ጊዜ ግምት ትክክል ሊሆን አይችልም ስለዚህም መንግስትንም  ሆነ ህዝብን ከህግ ውጭ የመጉዳትም የመጥቀምም አጋጣሚዎችን ሊፈጥር ይችላል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባም ሆነ የክልል የገቢዎች ቢሮዎችም አሁን ላይ የግብር የአሰባሰብ ስርዓታቸዉ፤በጥናት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በግምት ላይ በመሆኑ ዘመናዊ የታክስ አሰባሰብ ስረአት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም ዜጋ ግዴታዉን አዉቆ ህጋዊ ሃላፊነቱን የሚወጣበት ዘመናዊ የታክስ አሰባሰብ ስርዓት በመዘርጋት ላይ እንዳለ አቶ ጌታቸዉ ግርማ አስታዉቋል፡፡

መጋቢ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...