በኢራን የሚገኘው የዓለም ግዙፉ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራ ጥቃት ተፈጸመበት

Date:


  1. በኢራን ደቡብ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ስፍራ የሚገኘው የፔትሮኬሚካል ተቋም የአየር ድብደባ እንደተፈጸመበት ከእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል ዘገበ።
  2. ኳታር፤ እስራኤል በተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራው ላይ የፈጸመችውን ጥቃት “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” ስትል ኮንናለች።የታስኒም ዘገባ እንደሚያመለክተው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ረፋድ አካባቢ ነው።
  3. ከፊል ይፋዊው ፋርስ የዜና ወኩል በበኩሉ በቴሌግራም ገጹ ባወጣው ማስጠንቀቂያ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻው በእሳት መያያዙን ገልጿል። የእሳት እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በስፍራው እንደሚገኙም ጠቅሷል።
  4. በዓለም ትልቁ በሆነው የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ስፍራ ደቡብ ፓርስ ውስጥ የኳታር እና ኢራን ማምረቻ ተቋማት ይንቀሳቀሳሉ።ኳታር በመግለጫዋ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻው ስፍራ ላይ ጥቃት የተፈጸመው በእስራኤል እንደሆነ የገለጸች ሲሆን፣ ድርጊቱንም “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” ስትል አውግዛለች።
  5. የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማጅድ አል አንሳሪ፤ በኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ጥቃት “የዓለም የነዳጅ ደኅንነት ላይ ስጋት እንደሚደቅን” ተናግረዋል።
  6. “ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ወሳኝ ተቋማትን ዒላማ ከማድረግ መቆጠብ እንደሚስፈልግ እንገልጻለን” ያሉት ቃል አቀባዩ፤ “ሁሉም ወገኖች” ዓለም አቀፍ ሕግን እንዲያከብሩ እና ውጥረቱን ለማርገብ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
  7. BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...